በሁሉም እስቴት ስላሉ ትምህርት ቤቶች ጥናት በማድረግ ጥሩና መጥፎ የሚባሉትን በመለየት እናቀርባለን፡፡ ለተማሪዎችና ለአዲስ ምሩቃን ስኮላርሥፖችንና ኢንርን ስራዎችን የያዙ መረጃዎችን እናሰራጫለን፡፡ ወጣቶች በምን ትምህርት ኮሌጅ ገብተው ቢማሩ እንደሚሻልና የት ትምህርት ቤት ቢገቡ እንደሚሻል የምክር አገልግሎት እንሰጣለን፡፡ ስለወጣቶ በትምህርት የተሸለ ብልጫ እንዲያመጣ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በመስጠት ሴሚናሮችን እናካሒዳለን፡፡ ስለትምህርት ቤት ዙሪያ ስላሉን አዳዲስ መረጃዎች እናሰራጫለን፡፡ በሐገር ቤትና በተለያዩ የአለም ክፍሎች ያሉትን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በተምህርት ዙሪያ ሊጠቀሙበት የሚችሉትን መረጃዎች እናሰራጫለን፡፡በዚህ አገልግሎት አባላትን በመመልመል ያላቸውን ሐሳብ የሚያካፍሉበት የመጻጻፊያ ገጽ ይኖረናል፡፡ በዚህም መሰረት ሼር የተደረገው በማን እንደሆነና ተአማኒነቱ ይታወቃል፡፡