ሕብረት ተኮር አገልግሎት በመስጠት ወጣቶች በግላቸው የሚቸገሩበትን ነገር በሕበረት በመሆን ለራሳቸው ችግር ራሳቸው መፍትሔ እንዲያመጡ እናደርጋለን፡፡ በተጨማሪም የታመሙ ሰዎች አልጋ አንጥፎ በመምጣት፣ ግሮሰሪ በማድረግ፣ ምግብ በመስራትና በመሳሰሉት እንረዳለን፡፡ በዚህ ስር የሊትሬቸርና የስነጽሁፍ ዝግጅት በማድረግ መጸሐፍትን በማሰባሰብና የተለያዩ ውይይት እንዲደረግ እናደርጋለን፡፡ ለስነ ጽሑፍ ርእሶችን በመስጠት እናወያያለን በሎካል ቤተክርስቲያንና በመላው አሜሪካ ከዛም በመላው ኢትዮያን ጨምሮ ታላላቅ የስነጽሁፍ ውድድሮችን በእድሜአቸው እናደርጋለን፡፡