በዚህ የጽናት አገልግሎት ቤተክርስቲያንና የቤተከርስቲያን መሪዎች ተጠያቂነትንና ሐላፊነት ያለውን አገልግሎት እንዲያገለግሉና ምእመኑ ስለአገልጋዮቹ ምንነት፣ እምነት፣ ስራና የጽድቅ ኑሮ እየገመገመ የተገኙ መረጃዎችን በሙሉ ለምእመኑ ለማድረስ የታሰበ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የጽናት አገልገሎት ከማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ (በሚደግፈንም በማይደግፈንም) አመለካከት ነጻ ሆኖ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ድካምና ብርታት ለህዝብ በማሳወቅ ሕዝቡ የራሱን ጥንቃቄና እርምጅ እንዲወስድ ይፋ ያደርጋል እንጂ በማንም ውሳኔ ውስጥ ጣልቃ አይገባም፡፡ ይህ አገልግሎት በተጨማሪም ቤተክርስቲያንም ሆነች የቤተክርስቲያኒቱ መሪ ፈለገም አልፈለገም ስለቤተክርስቲያኒቱ፣ ስለመሪው አገልግሎቱ፣ ስለራእዩ፣ ስለቤተሰቡ (ትዳሩ)፣ ስለኑሮው (ለምሳሌ ሐብቱ) እና የመሳሰሉት በመንፈሳዊ ብቃቱ ላይ አዎንታዊና አሉታዊ ተጽእኖ ያላቸው ነገሮች ዝርዝር ይወጣል፡፡ በተቻለ መጠን መረጃዎችን ከአገልጋዩና ከቤተክርስቲያኒቱ ምእመኖች ለማግኘት ቅድሚያ በመስጠት የሚሰራጨው መረጅ እውነታነት የተረጋገጠ እንደሆን ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል፡፡

የጽናት አገልግሎት ቤተክርስቲያኖችንና አገልጋዮችን የምንገመግምበትን ሰፊ መመዘኛ ለአብያተክርስያነት በመበተንና ለምእመን በማድረስ፣ በሚዘጋጁ መመዘኛ መለኪያዎች መሰረት ስለአገልጋዮቹ ሕይወት ያለውን እውነታ በመረጃ መረባችን በመልቀቅ ምእመናኖች ከስህተት ትምህርት እንዲጠበቁ የሚያደርግና ግራና ቀኙን የማያውቀውን ህዝብ ከጥፋት ለመጠበቅ የታሰበ ነው፡፡ ስለአንድ አገልጋይና ስለሚመራው ወይም ስለሚያገለግልበት ቤተክርስቲያን በተቻለ ትክክለኛ መረጃ በማሰባሰብ እናሰራጫለን፡፡

ሰው በህይወቱ ዘመን ሁሉ ማቆም የሌለበት ነገር ቢኖር በሕይወቱ ዘመን ሁሉ አንዴት እንደሚኖርና እንደሚሻሻል መማር ነው፡፡ ስለዚህ ለቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች እንዴት ህዝቡን ማገልገል እንዳለባቸውና ራሳቸውን መገምገም እንደሚችሉ የአስተዳደር ስልጠናንና አጫጭር ትምርቶችን እናዘጋጃለን፡፡ ይሄም አገልግሎት ገና በጅማሬ ላይ ያለ እንደመሆኑ መጠን ተሳታፊዎች በሚሰጡን አስተያየትና ሒስ በመታገስ የተሻለ አገልግሎት ለመስጥት እንሞክራለን፡፡

በዘመናችን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አማኞች በከፍተኛ የመንግስት አመራር ላይ ስልጣን የጨበጡበት ዘመን ነው፡፡ በሐገራችን ላለው የተለያዩ መሰረታዊ ችግሮች መንግስት ጥፋተኛ ነው ስንል እነዚሀ ስልጣኑን ይዘው ግን ምንም ለውጥ ወይም ተጽእኖ ለማምጣት ያልቻሉትን ክርስቲያን ባለስልጣናትም እየከነናቸው ነው፡፡ እነዚህ ክርስቲያን ባለስልጣናት የክፉ መጣቀሚያ ሆኑ ማለት ደግሞ እነሱን ያሳደገችውና አያሳደገች ያለችው ቤተክርስቲያን መሰረታዊ ችግር አለባት ማለት ነው፡፡