ስለ ጉልበታችሁ አምላክ ቤተ ክርስቲያንን ተዉአት!

በወንድም ሰለሞን ጥላሁን /መጋቢ/ Sept 28, 2017 ከፌስቡክ የተወሰደ

በዚህ ደረጃ የምሰጠው አስተያየት በየቦታው ተከስቶ እንደሆነ ባላውቅም፣ ትኩረቴ በአንድ አካባቢ የተከሰተን አሳሳቢ ጕዳይን ይመለከታል፣

ያስተዋልኩት ነገር ቤተ ክርስቲያን የገዛ ልጇቿ ጉልቤ (Bullies) ሆነውባታል፣ ሁለተኛም ሊደግሙ የማይገባቸውን ስህተትም ፈጽመዋል፣ እንድል አስገድዶኛል፣ በምሰጠው አስተያየት ፍላጎቴ “ዐውቀን እንድንታረም” ብቻ ነው። በመሰረቱ እኔ ያስተዋልኳቸው ዓይነት ስብስቦች ራሳቸውንም ሆነ ሌሎችም እነርሱን እንደ ቤተ ክርስቲያን ላይቆጥሩ የሚችሉ ቢሆንም የቤተ ክርስቲያንን አንዳንድ ሚናዎችን በመንጠቅ ባስፈለገው ሰዓት ባስፈለገው ቦታ ከሚፈልጓቸው ሰዎች ጋር የሚፈልጉትን ነገር አድርገውና አስደርገው የሚያልፉ ናቸው። በየትኛውም መንገድ እናደርጋቸዋለን የሚሏቸው ተግባሮች፣ እንደ ወንጌል ስርጭት፣ የአካባቢ የጋራ አምልኮ፣ በጎ ላደረጉ ሰዎች ሽልማት መሸለም፣ የተጣሉ ማስታረቅ እና የመሳሰሉት ርእሳነ ጕዳዮች

የተጣሉ ማስታረቅ እና የመሳሰሉት ርእሳነ ጕዳዮች ላይ አተኳሪ  በመሆናቸው እና በዓይነታቸውም የአንድ ሰሞን ንቅናቄ አድርገው የሚሰወሩ ኃይላት በመሆናቸው ለዳኝነት አስቸጋሪ ናቸው። እነዚህ ኃይላት በአብዛኛው ጊዜ  ድብልቅ ፍላጎት ባላቸው ግለሰቦች የሚፈጠሩ በመሆናቸው ኑግና ሰሊጡ ስለሚደባለቅ ገንቢ አስተያየት እንኳ ለመስጠት አዳጋች ናቸው።

ማናችንም በእንዲህ ዓይነት ጉዳዮች ውስጥ ለመሳተፍ ወደ ኋላ የማንልባቸው በመሆናቸው በቀላሉ የሚከወኑ ናቸው። ስብስብ ድምጻቸው በሚከሰቱበት አካባቢ ጎድሏል ተብሎ የሚታሰብን “ጽድቅ”፣ “ፍትህ”፣ “ትድግና” (Leverag) የመሳሰሉትን አድራጊዎች እንደሆኑ ስለሚያስተጋባ፣ የዋሃንም ሆነ ድብቅ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በቀላሉና በፍጥነት ይከተሏቸዋል። ስለዚህ በበጎ ተጀምረው በክፉ ሊያልቁ ይችላሉ!

ይሁን እንጂ በአገልግሎት ውጤት፣ በነባርነት፣ በተከታይ ብዛት፣ የገዘፉ ቤተ ክርስቲያኖች ለእነዚህ ዓይነት እንቅስቃሴዎች አጸፋ ምላሻቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ስለሚታወቅ እምብዛም አይደፈሩም። እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያኖች  ውስጣቸው ሊፈጠር የሚችል ችግር ምንም ዓይነት ቢሆን ከውጪ አይደፈሩም ከውስጥም ሊነሳ የሚችል

ሊፈጠር የሚችል ችግር ምንም ዓይነት ቢሆን ከውጪ አይደፈሩም ከውስጥም ሊነሳ የሚችል አድማ ነክ እንቅስቃሴ ቢኖር እንኳ እዚያው ኮሪደር ላይ ይመክናል!!! የተበታተነ ኃይል ባላቸው አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ጉልቤዎች (Church Bullies) ከልካይ የላቸውም፣ ተጠቃሁ ባይ ያሰባስባቸዋል አጥቂ ተብየውን ማህበርም ሆነ ግለሰብ ሰቅለው ለተበዳይ ተብዬ ትንሣኤ አውጀው ይሔዳሉ፣ በቃ ይኸው ነው ጨዋታው፣ ያስተዋልኩት ይህንን እጅግ አሳዛኝ ድርጊት ነው!። ልክ አይደለም፣ መደገምም የለበትም ብዬ አምናለሁ፣ “ስለጉልበታችሁ ብላችሁ ተዉ” ብዬም እለምናለሁ! እንዲህ ዓይነት ቡድኖች የተግባሮቻቸው ገጽታ በራሱ እና በራሱ ብቻ ሲታይ ቅን ስለሚመስል ለወቀሳም ለሙገሳም አስቸጋሪ ነው፣ ከዚህም በተጨማሪ በየክስተቱ የሚሰለፉት ሰዎች ወይ በአገልግሎት ተሞክሮ፣ ወይ በትምህርት ዘለቅነት፣ ወይ በነባርነት ወይም እንደ ገንዘብና ሥልጣን ባሉ በተመሳሳይ ማሕበራዊ እሴቶች የሚታወቁ ግለሰቦች በመሆናቸው በየአካባቢው በሚፈጠረው ችግር የፈጥኖ ደራሽ ጣልቃ ገብነታቸው ወዲያው ተቀባይነት ማግኘት ይችላል፣ የተጽእኖ አቅማቸው ግን እንደ የአካባቢው ይለያያል። አንዳንድ አካባቢዎች ትሥሥራቸው ጠንካራ ስለሆነ በቀላሉ አይደፈሩም። በግራም ሆነ በቀኝ ወደውም ሆነ ሳይወዱ፣ አስበውበትም ሆነ ሳያስቡ ግን በውጤቱ ተግባራቸው

አስበውበትም ሆነ ሳያስቡ ግን በውጤቱ ተግባራቸው በአብዛኛው አፍራሽ ነው፣  አሰራራቸው ጀምስቦንዳዊ ነው  በድንገት ከፓራሹት እንደሚወርድ ይወርዳሉ፣ ባጭር ጊዜ ተደራጅተው የሚፈጽሙትን ፈጽመው ወደ ቀዬአቸው ይመለሳሉ …. ይኽ አሰራር በዚህ የሚቀጥል ከሆነ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያኖች ራስ ገዝ (Autonomies) ሆነን እንቀጥላለን ብለው ማሰብ ማቆም አለባቸው፣ ምክንያቱም እነርሱ ያላደራጁት የውጪ ኃይል ለዚያውም የአማኞች ስብስብ በድንገት ሊዘምትባቸው ይችላል! ይህንን በሚመለከት በምኖርበት አካባቢ እጅግ እጅግ አሳዛኝ ክስተት ተመልክቻለሁ እያልኩ ነው።

እንዲህ ዓይነት ኃይል ለመሆን የሚያስፈልጉ አብይ መስፈሪያዎች የሚከተሉት ናቸው፦ 1) የተጨቋኝ/ተገፋሁ ባይ ትራኬ (Appealing narrative of the “oppressed”) 2) የጨቋኝ ተብየው ስሱ ጎን (Vulnerability of the so called “oppressor”) 3) የዘመቻ ፊት አውራሪዎች (Vanguards for a campaign) 4) በምግባራቸው ግብ እንጂ መርህ ጠያቂ ያልሆኑ አስተባባሪዎች (Pragmatic and goal oriented individual coordinators) 5) ኃይል፣ ሥልጣን፣ ታዋቂነት፣ ተጽእኖ ፈጣሪነትን የተጠሙ አንደበተ ርቱአንና ደፋር ተግታጊዎች

5) ኃይል፣ ሥልጣን፣ ታዋቂነት፣ ተጽእኖ ፈጣሪነትን የተጠሙ አንደበተ ርቱአንና ደፋር ተግታጊዎች (Power mongers, cheap popularity seekers,…) እነዚህ ራሳቸውን ሰውረው ሊቀላቀሉ ይችላሉ።  6) ጥቂት የዋሃን አጃቢዎች (Few innocent crowed) 7) ሌሎች ፍጆታዎችና የግለሰብ ዓይነቶች እንደ አስፈላጊነቱና በየደረጃው ጥቅም ላይ ይውላሉ፣ ዘመቻው ይዘመታል የተፈለገው ግብ ዘንድ ይደረሳል:: ከዚያ በኋላ በሚኖሩ እንቅስቃሴዎች “ተመልካች አለ”፣ “ተሳስተን ሊሆን ይችላል”፣ “የምንሰራው ስራ የረጅም ጊዜ ችግር ይፈጥራል”፣ “ተዉ የሚሉንን ሰዎች እንስማ” እና የመሳሰሉት አስተሳሰቦች የሌሉበት ቡልዶዘራዊ አካሔድ መሔድ ነው፣ እንግዲህ ቤተ ክርስቲያን ምን ታደርጋለች? ግራ ይገባታል፣ ተጨማሪ ጭንቀት መሪዎች ይጨነቃሉ፣ አባላት አንድ ወጥ ድምጽ መስማት ያቅታቸዋል ይረበሻሉ፣ አንዳንድ ሰዎች ይታመማሉ ….የተጀመሩ ስራዎች ይስተጓጎላሉ፣ በውጤቱም ዚሮ ሰም (Zerosum)  ድምዳሜ ላይ ይደረሳል።

ይህ ቃል የሰላም ግንባታ ባለሙያዎች የሚጠቀሙበት ቃል ነው፣ ዋናው ቁም ነገር የግጭት ባለ ድርሻዎች በማንኛውም የድርድር መንገዶች አለመስማማት ላይ ሲደርሱ “አልቦ ግብ ድርድር”

ባለ ድርሻዎች በማንኛውም የድርድር መንገዶች አለመስማማት ላይ ሲደርሱ “አልቦ ግብ ድርድር” ላይ ለመቆም ይወስናሉ (አልቦ ማለት ዜሮ ማለት ነው)። በዚህም ቡድኖች በሙሉ ይከስራሉ፣ ይሁን እንጂ አንደኛው ወገን የሚጠቀመው ከሌላው ወገን በሚቀነሰው ነገር ነው፣ ባጭሩ “ጥቅሜ ያለው ጉዳትህ ውስጥ ነው” ማለት ነው፣ ወይም “ጉዳትህ ጥቅሜ  ነው” እና “ኪሳራህ ትርፌ ነው” የሚል የግጭቱ ባለድርሻዎች አይቀሬ ጉዳት ላይ ያተኮረ የግጭት መፍትሒ ነው። እንዲህ በመሆኑ የግጭት ባለድርሻ አረጋግጦ መሔድ የሚፈልገው ጥቅሙ የሚመሰረተው በሌላኛው ወገን ጉዳት ላይ መሆኑን ነው። በፖለቲካውና በንግዱ ዓለም ይህንን ምርጫ ለመምረጥ የሚገደዱበት ጊዜ አለ። በአማኙ ማህበረሰብ ግን ሊታሰብ አይገባም፣ እነሆ ግን ተከስቶ አይቻለሁ፣ እንዳይደገም እለምናለሁ።

በሁላችንም ዘንድ እንደሚታወቀው ሁሉ በዚህ በዝርወታዊው (Diaspora community) ማሕበረሰብ የአገሬ ሰው የሚያደርገው ማንኛውም ማህበራዊ ስብስብ ውዝግብና ግጭት የሞላበት ነው፣ ይህ የማንክደው አሳዛኝ ክስተት ነው፣ እንዲህ ዓይነቱ ጕዳይ ጫፌንም አይነካኝ የሚል ለመሰባሰብ ያልሞከረ ብቻ ነው። ከስፍራ ወደ ስፍራ፣ ከአገር አገር፣ ከባሕል ወደ ሌላ ባሕል፣ ከታሪክ ወደ ሌላ ታሪክ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት ተወልደው ካደጉበት ቤተ ክርስቲያን ወደ ሌላ አዲስ ቤተ ክርስቲያን እና

በመንፈሳዊ ሕይወት ተወልደው ካደጉበት ቤተ ክርስቲያን ወደ ሌላ አዲስ ቤተ ክርስቲያን እና በመሳሰሉት የዝውውር ሒደቶች (Transition process) የሚከሰቱ ሽግግር ወለድ ችግሮች ከግለሰብ አንስቶ እስከ ማሕበራዊ ስብስቦች ድረስ የሚንጸባረቁ መሆናቸው እጅጉን ግልጽ ነው። ይህ ዝርወታዊ ማህበረሰብ ከቤተ ሰብ ስብስብ፣ የፖለቲካና የሃይማኖት ስብስቦችን ጨምሮ፣ በየስቴቱ የተወሳሰቡ ውዝግቦችን የሚያሳልፍ ህብረተሰብ ነው። ስለዚህ በርካታ የግጭት ሰበቦች (Causes of conflict) ፣ የግጭት አሻቃቢ ምክንያቶችና ( Escalation of conflict) የግጭት አፍጣኝ ምክንያቶች (Accileration of conflict) ይታዩበታል፤

በግሌ እንደተመለከትኩት፣ ግጭቶች በተገቢው መንገድና ጊዜ ተይዘው መፍትሒ እንዳያገኙ መሪ እንቅፋት ሆነው የሚታዩት ከግጭት ሰበቦች ይልቅ ግጭት አሻቃቢና አፍጣኝ ምክንያቶች ናቸው። እነዚህም ምክንያቶች በርካታ ሲሆኑ፣ በዚህ አጭር የአስተያየት ጽሑፍ አተታቸውን መግለጽ ባይቻልም ዝርዝራቸው ግን የሚከተለውን ይመስላል፦ 1) ግጭት አሻቃቢ  ፉክክራዊ የግጭት አያያዞች  በመፍትሔ ፍለጋው ሁሉን ግለሰብ አቀፍ ያለመሆን ችግር

በመፍትሔ ፍለጋው ሁሉን ግለሰብ አቀፍ ያለመሆን ችግር  ፍትህን በሚመለከት ያሉ የትርጕም ልዩነቶች  የድርጊት ሰበቦችን (ሞቲቭን) በተሳሳተ መልኩ መገንዘብ  በመፍትሔ ፍለጋው ሁሉን ጉዳይ አቀፍ ያለመሆን ችግር  በመፍትሔ ፍለጋው የተቀናቃኝ ወገንን አማራጮች ያለማየት ችግር  “አሳደህ በለው” መፍትሔዎች  ግጭትን በራሱ እንደ ችግር መቁጠር  በቂ ያልሆነ የመረጃ አሰባሰብ መንገድ 2) ግጭት አፍጣኝ ምክንያቶች  ምን አገባኝ ማለት  ለተፈጠሩ አለመግባባቶች ተስማሚ የሆኑ የግጭት ማስተናገጃ መንገዶችን ለይቶ አለማውጣት  በግንኙነት ሒደት ውስጥ ለተነገረው ነገር የተሳሳተ ትርጉም መሥጠት  መደባበቅና ማታለል  የሚያቆስል ንግግር  በቂ ያልሆኑ የመረጃ ማሰባሰቢያ መንገዶችና ግጭት አያያዙ ከሚጠይቀው ጊዜ በታች መጠቀም  አዲስ የሆኑና በቂ መረጃ የሌላቸው ተሳታፊዎች  መገናኛ ብዙሃን የሚያጦዙአቸው ግጭቶች  ያለፈ ግጭትን ታሪክ አሁን  ካለው ውዝግብ ጋር ግንኙነት እንደሌለው መቁጠር   ከተግባቦት ጋር የተገናኙ ግጭት ነክ ችግሮች

ግንኙነት እንደሌለው መቁጠር   ከተግባቦት ጋር የተገናኙ ግጭት ነክ ችግሮች ለተግባቦት ባሕል ነክ ችግሮች  የቋንቋ ልዩነቶች  የፍላጎት ግጭት/ የተአማኒነት መጉደል – ማመን አለመቻልም ሆነ አለመታመን

ለሁላችንም ግልጽ እንደሆነው ሁሉ፣ በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ቤተ እምነት ከቤተ እምነትም (Intergroup Conflict የቡድኖች ግጭት) ሆነ በአንድ ቤተ እምነት ውስጥ እርስ በርስ ግጭት (Intragroup Conflict ውስጠ-ቡድን ግጭት) ይፈጠራል፣ የዚህ ምክንያቱ በአብዛኛው፣ አስተዳደር፣ አስተምህሮ፣ የመሪዎች ምግባር፣ የመረጃ እጥረት ወይም የመረጃ ትርጉም ልዩነት፣ የመሪዎች ባሕሪ፣ የተግባቦት ችግሮች፣ የግብ አፈጻጸምና የግብ ልዩነቶችም ጭምር እና ከዚህም በላይ ናቸው። ይህም ቤተ ክርስቲያን በአዲስ ኪዳን ከታየችበት ከመጀመሪያው መጽሐፍ የሐዋ ሥራ ምእራፍ ስድስት አንስቶ ምእራፍ 15 ሙሉውን ጨምሮና በአብዛኛው መልእክቶችም ጭምር የተንጸባረቀ ኃጢአተኞች በክርስቶስ ጽድቅ ተሰብስበው ባሉባት ማሕበር ሁሉ የሚታይ ኗሪ ክስተት ነው፣ ባንፈልገውም አለ፣ እንደሌለ መቁጠርም ሆነ ሲከሰት መደናገጥ ከእውነታው ዓለም ያወጣናል። በአግባቡ የተያዙ ግጭቶች ሁሉ ከጉዳታቸው ጥቅማቸው ሲያመዝን

ከእውነታው ዓለም ያወጣናል። በአግባቡ የተያዙ ግጭቶች ሁሉ ከጉዳታቸው ጥቅማቸው ሲያመዝን በተቃራኒው ደግሞ ጸብ መራሽ ግጭቶች (Antagonistic Conflicts) ደግሞ የቤተ ክርስቲያንን ገጽታና ተልእኮ በእጅጉ ይጎዳሉ!

ከዚህም የተነሳ በአገራችን ኢትዮጵያ በቤተ ክርስቲያኖች መካከል ሆነ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተፈጠረ ግጭቶች የራሳቸውን ችግር ከመፍታት አንስቶ እስከመገንጠል ድረስ የደረሱ በርካታ ተሞክሮዎችን ቤተ ክርስቲያን አሳልፋለች፣ ከዚህም ጋር አብዛኛው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሶስተኛ ወገን መካከለኛ በመግባት ግጭቶችን የመፍታት ባህል ያላት ቤተ ክርስቲያን ናት፣ ይህ በማይሆንበት ጊዜ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ አሰራሮች ለቤተ ክርስቲያኒቱ እንደሚተው በሁሉ ዘንድ የታወቀ ሆኖ ኖሯል። ቤተ ክርስቲያኖች “ራስ ገዝ” (Autonomous) ናቸው ተብሎም ስለሚታመን መንግሥት እንኳ ከሕግ ጋር ተያያዥ አስካልሆነ ድረስ ጣልቃ አይገባም፣ ከመሪዎች አንስቶ አባላትን ጨምሮ ያሉ ግለሰቦች በግለሰብነት ደረጃ ከአጠቃላዩ ማሕበር ስለሚያንሱ የቤተ ክርስቲያን ውሳኔ የተባሉ ውሳኔዎች ሁሉ እንደ መንፈሳዊ ሥልጣን ታስበው ይከበራሉ፣ ይተገበራሉ ያልተስማማው ደግሞ ይለያል፣ ይተዋል፣ ይሔዳል ከዚህ ውጪ የሚደረግ እንቅስቃሴ ሁሉ ግን ….ሕብረትን ያፈርሳል፣ ግጭትን

እንቅስቃሴ ሁሉ ግን ….ሕብረትን ያፈርሳል፣ ግጭትን ያሻቅባል፣ በሰነበተ ቁጥር ደግሞ አማኝ ላልሆነው ማሕበረሰብ የቤተ ክርስቲያንን ገጽታ አቆሽሾ ያሳይል፣ ለባሰ ክፉ ነገር አሳልፎ በመስጠት ሰይጣንን ያስደስታል፣ ጌታን ያሳዝናል፣ ተልእኮን ያደናቅፋል…. በአጠቃላይ ልክ አይደለም!

 

በማንኛውም መልኩ በሶስተኛ ወገን ገለልተኛነት የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶች ዓይነተኛ ባሕሪያቸው አስገዳጅ አለመሆናቸው ነው፣ ደግሞም የግጭት ተሳታፊዎችን ሁሉና እኩልና በፈቃደኛነት ላይ ተመስርቶ ያሳተፈ መሆኑ ነው። ከዚህ ውጪ ሲሆን አስገዳጅ ነው ጉልቤነት ነው ። ሚዛናዊ የሆነ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እናደርጋለን ከተባለ ግን ቢያንስ የሚከተሉትን ግንዛቤዎች ከግምት ውስጥ መክተት ይገባል። በግጭት ጊዜ ጣልቃ አገባብ (Intervention) ጥንቃቄ የሚፈልግና ራሱን የቻለ ገለልተኛነት የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ የራሱ ሥርዓትና ስልት አለው።  ይህንን ያገናዘቡ ተቋማት በልማት ስራ ስምሪታቸው እንኳ ለልማት ሥራ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት “ተጨማሪ ጕዳት አትፍጠር” (Do no more harm) የሚል መርህ አላቸው፣ ይህም ማለት “ልማቱ ያስፈለገበት ጕዳይ ካስከተለው ጉዳት የበለጠ ለልማት የምንሰራው ሥራ ሕዝቡን እንዳይጎዳ” የሚል መርህ አላቸው። ለምሳሌ

ካስከተለው ጉዳት የበለጠ ለልማት የምንሰራው ሥራ ሕዝቡን እንዳይጎዳ” የሚል መርህ አላቸው። ለምሳሌ በአንድ አካባቢ “ለተላላፊ በሽታ ምክንያት የሆነው የመጸዳጃ ስፍራ ባለመኖሩ ነው” የሚል ቅን እና የልማት አስተሳሰብ በተግባር መዋሉ በሌጣው/ በጥቅሉ/ ሲታይ እሰየው የሚያሰኝ ነው፣ ከወራት በኋላ ግን የአካባቢው ገበሬ በዓይጥና በዝንጀሮ መንጋ የተጎዳው አዝመራውን የልማት ድርጅቱ ያዘጋጀለት የሲሚንቶ መጸዳጃ ቤትን እንደ ደህና ጎተራ ቢቆጥርና እህሉን ቢከት መጸዳጃው ወደ ጎተራነት ሲቀየር አባወራዎቹ በባለቤትነት ውዝግብ አካባቢያዊ ጦርነት ቢያስነሱ ከተስቦው ችግር ይልቅ የመጸዳጃው ግንባታ የፈጠረው ችግር ባሰ ይባላል። ይህ መርህ በግጭትም ጣልቃ ገብነት ልብ መባል ያለበት አስፈላጊ መርህ ነው፣ ምክንያቱም ቀዳሚው ግጭት ከፈጠረው ችግር ይልቅ የተሳሰቱና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ጣልቃ ገብ እንቅስቃሴዎች የሚፈጥሩት ግጭት፣ የግርሻ ውጤቱ (Relapsing effect) የከፋ ስለሚሆን ነው። እንዲህ ዓይነቱ ነገር በመጀመሪያ ደረጃ ለግጭቱ ቀዳሚ ባለድርሻዎች (Primary stakeholders) ነገረ ግጭታቸውን አንድም በአግባቡ አይፈታውም አንድም ደግሞ ያጦዘዋል! ከዚህ የተነሳ የሚከተለውን ማሳሰብ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ።

ሰዎች ጣልቃ ሲገቡ ቢያንስ የሚከተሉት መሰረታዊ

ሰዎች ጣልቃ ሲገቡ ቢያንስ የሚከተሉት መሰረታዊ አስፈላጊ ነገሮች ሊሟሉ ይገባል (ከዚህ በታች ያለው ዝርዝር ለጅማሬ ያህል እንጂ በቂ ላይሆን ይችላል )  እኩላዊ የባለ ድርሻዎች ፍላጎትና ፈቃደኛነት (Willingness of parties)፣ በህግ ፊት በክስ እስካልቀረበ ድረስ የሰላም ግንባታ መንገድ ሙሉ በሙሉ በፈቃደኛነት ላይ የተመሰረተ ነው። በመሰረቱ የሰላሙ ሒደት የሚጀምረው እዚህ ዘንድ ነው! ቢያንስ የሚከተለው መሪ ግንዛቤ ያስፈልጋል፦

የማስማማት መርሆች • ለመስማማት መፈለግንም ሆነ አስማሚውን የሚመርጡት በግጭት ውስጥ ያሉት ግለሰቦች ናቸው • ፍጻሜውን የሚወስኑት ባለጕዳዮቹ ናቸው!!! • አስማሚው ሒደቱን ይመራል እንጂ በጕዳያቸው ላይ የራሱን ተጨማሪ ድጋፍ አያደርግም • አስማሚው “ይህን ያደረገ ይህ ይከተለዋል” የሚል ብያኔ ሰጪ አይደለም • የመስማማት ሒደት ውስብስብ ለሆኑ ችግሮች ፈጣንና ቀላል እንዳልሆነ መታወቅ አለበት!!! • የማስማማት ሒደት መደበኛ በሆነ መልኩ ሲፈጸም ራሱን የቻለ ሙያ ነው።

እኩላዊ የባለድርሻዎች ተሳትፎ (Equal participation)፣ የግጭቱ ባለድርሻዎች

እኩላዊ የባለድርሻዎች ተሳትፎ (Equal participation)፣ የግጭቱ ባለድርሻዎች በመፍትሒው ሒደት ላይ እኩል ተሳታፊ መሆን አለባቸው። ግጭት በባሕሪው በስማ በለው የሚዳኝ አይደለም።

በቂ የግጭቱ ስሌት (Enough analysis of the conflict) – የአንድ ግጭት መፍትሔ የሚወሰነው ቡድኑ ግጭቱን ያሰላውን ያህል ነው። ጣልቃ ገቢዎች ከሁሉም ወገን መስማታቸው ወደ ማስላት ሊያደርሳቸው ይገባል፣ በደንብ የተሰላ በአብዛኛው የተሻለ መፍትሒ አለው። (A well analyzed conflict is likely to produce transformative result)

ጎጂና ተጎጂ በሚገባውና በቅደም ተከተል ተለይተው ታውቀዋል ወይ? (Identify victim and perpetrator) እዚህ ጋ የሚወሰኑ ውሳኔዎች በሁሉ ዘንድ እኩል ስምምነት ካልተደረሰባቸው፣ ከዋናው ግጭት ውጪ ያሉ ተመልካቾችን ሁሉ ወደ ግጭቱ ተሳታፊነት የሚጋብዙ ስህተቶች ይፈጠራሉ።

ተገቢና አድሎ የሌለው የመስተናገሪያ (Mediation process) ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የግጭት ባለድርሻዎች መካከል ደረጃውን የጠበቀና በሒደት

ገብነት በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የግጭት ባለድርሻዎች መካከል ደረጃውን የጠበቀና በሒደት ውጤቱ የሚጠበቅ ንግግር ስለሆነ የሚያነጋግሩ ሰዎች (አስተናጋሪዎች) ተገቢ የሆኑና አድሎ የሌላቸው ሊሆኑ ይገባል።

ግልጽ የሆነ ሊደረስበት የተፈለገ ግብ (Objective of the intervention) ጣልቃ በመግባት ሊደረስ የተፈለገው ግብ በግልጽና በዝርዝር ምንድን ነው?

የተጠያቂነት እቅዶች (Accountability plan) በሒደቱ እውነት በተገለጠ ጊዜ ቡድኖች ተጠያቂ የሚሆኑበት መንገድ ተዘጋጅቷል ወይ?

የማካካሻ እቅዶች (Restitution plan) የበደለና የተበደለ በተገኘበት ጊዜ ምን የማካካሻ መንገድ ተዘጋጅቷል?

የመደምደሚያ ሥርአት (Proper closure) ፍጻሜው ሕዳሴአዊ የሚሆነው እንዴት ነው?

############################# ###^

የሚሰማ ካለ ተጨማሪ ማሳሰቢያ

  1. አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ትከበር፣ አትናቅ፣ ከእኛ
  2. አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ትከበር፣ አትናቅ፣ ከእኛ የቀደሙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በሌሎች አጥቢያዎችና በመሪዎቻቸው ላይ አይዘምቱባቸውም ነበር፣ ለበጎ ሥራ እንኳ የምናደርገው ጣልቃ ገብነቶች ጥንቃቄ አይጕደላቸው። ከስሜታዊነታችን ይልቅ ምክንያታዊነታችን ይቅደም።
  3. ግጭቶች ልንገምተው ከምንችለው በላይ ፍጹም ውስብስብና ብዙ ገጽታ አላቸው፣ በጥቂት ጥቅሶች አመናፍሰን የምናስወግዳቸው እንዳልሆኑ ቢያንስ ከረፈደብን በኋላ እንኳ እንወቅ።
  4. ሁላችንንም ግድ የሚሉን ነገሮች ብዙና ተመሳሳይ ቢሆኑም ምንም ዓይነት በእውቀትና በአገልግሎት ተሞክሮ ከፍ ያለ እርከን ላይ ብንሆንም እንኳ የሁላችንም ተጽእኖ እኩልና አንድ ዓይነት እንዳልሆነ እንወቅ፣ ከእነዚህ ነገሮች በመነሳት የምንፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ በፈለግነው ቦታ ሁሉ ማድረግ የምንችል እንዳይመስለን እንጠንቀቅ፣ ይህም አስተሳሰብ በአንዳንዶች ዘንድ በጊዜ መወገድ አለበት ብዬ በትህትና አሳውቃለሁ።
  5. በጓደኝነትና በአገልግሎት መካከል፣ ያሉ ልዩነቶችን ጠንቅቀን እንወቅ፣ ጓደኝነት የተከበረና ለብዙ ነገር የሚጠቅም ቢሆንም፣ በግጭቶች ጊዜ ሶስተኛ ወገን

ጠንቅቀን እንወቅ፣ ጓደኝነት የተከበረና ለብዙ ነገር የሚጠቅም ቢሆንም፣ በግጭቶች ጊዜ ሶስተኛ ወገን ነጻ መካከለኛ ሊያደርግ የማይችል እንደሆነ እንገንዘብ!  የጠበቀ ወዳጅነት ባለበት ግንኙነት ውስጥ ገለልተኛ ነን ብሎ ለማለት ማንም መድፈር የለበትም።

  1. በቤተ ክርስቲያን ያሉ ሒደቶችን በትእግስት እንጠብቅ፣ ሁሉም ነገር ቢመለከተንም ሁሉም ነገር እኩል አያገባንም፣ ወራትና ዓመታት ያስቆጠሩ ችግሮችን በአንድ ጀንበር እኛ በምንፈልገው መንገድ ለመፍታት መሞከር የሚጎዳ የዋህነት ነው። ፍትሕ ጎድሏል ብለን በምናስብበት ሁኔታ ውስጥ እንኳ ስንገኝ እግዚአብሔር በሒደት ውስጥ ለሚሰራው ሥራ ትእግስት ይኑረን! ጌታን እንዳንቀድም!!!
  2. በተወሳሰቡ ግጭቶች መካከል አግባብ ከጎደልውና ከወንገንተኛ ጣልቃ ገብነት መቆጠብ ያስፈልጋል፣ ቤተ ክርስቲያን ከግለሰብ ትበልጣለች፣ ትልቅና ቋሚ ናት፣ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጥሮ ለሰው ልጆች በኃላፊነት እንዲያስተዳድሯት እንደሰጠ፣ ቤተ ክርስቲያንንም በደሙ ዋጅቶ በኃላፊነት እንዲያስተዳድሩ ለሰው ልጆች ሰጥቷል፣ በሁለቱም ኃላፊነቶች መጨረሻ ላይ የሚጠይቀው የፍጥረትም የቤተ ክርስቲያንም ፈጣሪ እንዳለ እንወቅ!!!

እንወቅ!!!

  1. “መሪዎችና የሰውነታችን የራሱ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት ሁለት ተመሳሳይ ስህተቶች ይፈጥራሉ አንዳንዴ ጥቃትን ሊከላከሉ ሲገባ ያስጠቃሉ አንዳንዴ ደግሞ ማጥቃት የማይገባቸውን ያጠቃሉ፡፡” የካንሰር በሽታ ማለት ባጭሩ፣ የታማሚው ሰው ሴሎች (ሕዋሳት) በራሱ በታማሚው ላይ ሲዘምቱበት ነው። ስለ እግዚአብሔር ብለን እባካችሁ አንዳንድ ወገኖች በቤተ ክርስቲያን ላይ በጽድቅ ስም አንዝመት!
  2. ቤተ ክርስቲያን በውስጧም በሚያጋጥሟት ችግሮች ሆነ ከውጪ በሚፈጠሩ ችግሮች ከተለኮዋ እንዳትዘናጋ ልትጠነቀቅ ይገባል፣
  3. ቤተ ክርስቲያን በማንኛውም ዓይነት መልኩ ከአጸፋ ምላሽ ልትጠነቀቅ ይገባል!

እንደ አንድ ግለሰብ ልመናዬ እባካችሁ ስለ ጉልበታችሁ ቤተ ክርስቲያንን ተዉአት!