በምድራችንና በመላው የአለም ክፍሎች ተበትነው ያሉ በወንጌል ስራ ዘመናቸውን አሳልፈው ሩጫቸውን በጽድቅ ያገባደዱ ቅሬታዎች እግዚአብሔር አሁንም አሉት፡፡ በእነዚህ ወገኖች ደጋግመን ተገልግለናል፣ ደጋግመን ተጽናንተናል፣ በእነርሱ ስለተገለጠው ጸጋ ጌታን አመስግነናል፡፡ በዚህ ክፍል ከቀዳሚው ትውልድ መሃል በሃገርና ከሀገር ውጭ የሚገኙ (አሁንም የሚያገለግሉ)፣  ከጌታ የተሰጣቸውን ጸጋ ለቤተክርስቲያን እየሰጡ ያሉ፣ ፍሬአቸው የተገለጠ፣ በተለይ በኑሮአቸውና በአካሔዳቸው ምሳሌ የሆኑንን አገልጋዮች የምናበረታታበት አምድ ነው፡፡ ይህ ድህረ ገጽ ጅማሬ ላይ ያለ እንደመሆኑ መጠን በዚህ አምድ ስማቸውንና ስራቸውን ለማስፈር የምትፈልጉትና አገልጋዮች ስም፣ የአገልግሎት ስፍራና ልናመሰግናቸው ያሰፈለገበት ጥቂት ሐሳቦችን እንድትልኩልን እንጠይቃለን፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት አገልጋዮች ለጅማሬ እንዲሆን የሰፈሩ ሲሆን በቀጣዩ ሌሎችንም ለማውጣት የእናነተን ትብብር እንጠይቃለን፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ መዲና እና የተለያዩ ክፍላተ ሐገራት ያሉትን የእምነት አባቶች ስም እና አገልግሎት በ Tsinat.org@gmail.com ብትልኩልን እናስተናግዳለን
1. ፓስተር ቶሎሳ ጉዲና
2. ፓስተር ታምራት ሀይሌ
3. ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ
4. ፓስተር ተስፋዬ መልካሙ
5. ወንድም ንጉሴ ቡልቻ