“Character cannot be developed in ease and quiet. Only through experience of trial and suffering can the soul be strengthened, ambition inspired, and success achieved” Helen Keller

በተለያየ የአእምሮ አካልና ችግር ያለባቸውን ወጣቶች በወንጌል በመድረስ ያላቸውን ችሎታ በተግባር እንዲተረጉሙት ለማገዝ፡፡ ይህ አላማ እነዚህን ወጣቶች መርዳት ሳይሆን ወጣቶቹ ያላቸውን እውቀትና ችሎታ ተጠቅመው ለራሳቸውና ለህብረተሰቡ ለውጥ ያለው ስራ እንዲሰሩ ማስቻል ነው፡፡ የህ ማለት ደግሞ ወጣቶቹን ከተረጂነት ወደረጂነት ለማሳደግ የታሰበ አገልግሎት ነው፡፡ በአለማችና ላይ ከራሳቸው አልፈው ለሰው ልጆች ከፍተኛ ለውጥ ያመጡ የአእምሮና ያካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ብንመለከት በፖሊዮ በሽታ አካለ ስንኩል የነበሩትና ለበርካታ አሉታዊ ለውጦች ማክናያት የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ፍራንክሊን ሮስቬልት፣ አይነስውርና ደንቆሮ የነበረችው ሔለን ኬለር እና በኮለራዶ ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ሳይንስ ተመራማሪና ለእንሰሳት እርባት ድርጅቶች አማካሪ የነበረው ዶክተር ቴምፕል ግራንዲን የአእምሮ ዝግመት (ኦዉቲስቲክ) ችግር ያለበት እንደምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በሐገራችን የተለያየ ችግር ያለባቸው ወጣቶች አንድም ከእውቀት ማነስ ሌላም ከአመቺ ሁኔታ አለመኖር የተነሳ በብዙ ነገር ተጎድተው ሕይወታቸውን በሙሉ የሰው ጥገኛ ይሆናሉ፡፡ የዚህ አገልግሎት ዋናና ተቀዳሚ አላማ እንደዚህ ያሉ ወጣቶች ቢሆኑም ወላችም ተገቢውንና ትክክለኛ አውቀት እንዲያገኙ ትምርቶችንና የእርዳት ምንጮችን ያፈላልጋል፡፡